May 21, 2024
ለእይታመዝናኛሞዛይክ

ሳይንስ ውሾች ሰዎችን እንደሚናፍቁ እና ከባለቤቶቻቸው ጋር ሲገናኙ እንደሚያነቡ ይናገራል

በ2022 በጃፓን የአዛቡ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ክፍል በዶ/ር ታከፉሚ ኪኩሱይ (Dr. Takefumi Kikusui) የተመራው ጥናት ውሾች ከባለቤቶቻቸው ጋር ሲገናኙ እንባ ያነባሉ ይላል። የዚህ ስሜታዊ የሆነ ምላሽ ምክንያቱም ኦክሲቶሲን ሆርሞን ነው፣ በሌላ ስሙ የፍቅር ሆርሞን ተብሎ የሚጠራው፣ የሰውና-የውሻ ግንኙነትን ያጠናክራል።

ጥናቱ 22 ውሾችን እና ባለቤቶቻቸውን ያካተተ ሲሆን ከመገናኘታቸው በፊት እና በኋላ እንባዎችን በመለካት በውሾች እና በሰዎች መካከል ያለውን ልዩ ትስስር ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ሰጥቷል።

ዶ/ር ኒኮላስ ዶድማን፣ የውሻ ባህሪ ጥናት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ጥናቱ አስደናቂ ሆኖ አግኝተውት በሰዎች እና በውሾቻቸው መካከል ያለውን ልዩ ግንኙነት እምያረጋግጥ ነው ብለዉታል።