May 21, 2024
ዜና

ትዊተር ሳውዲ አረቢያ የሰብአዊ መብት ረገጣ እንድትፈጽም በመርዳት ተከሰሰ

በተሻሻለው የአሜሪካ ክስ፣ ቀድሞ ትዊተር ተብሎ የሚጠራው እና አሁን “ኤክስ” እየተባለ የሚጠራው የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሳውዲ አረቢያን በተጠቃሚዎች ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመርዳት ተከሷል። ትዊተር የተጠቃሚውን መረጃ ከሌሎች ሀገራት በበለጠ መጠን ለሳውዲ ባለስልጣናት አሳልፏል ሲል ክሱ ያትታል።

ትዊተር በፋይናንሺያል እና በፖለቲካዊ ምክንያቶች የሳዑዲ አረቢያ መንግስትን እንደረዳው ክሱ ይገልፃል። ይህ ሁኔታ የተፈጠረዉ የሳውዲ ፍርድ ቤት በትዊተር እና በዩቲዩብ እንቅስቃሴው ላይ ተመስርቶ በአንድ ሰው ላይ የሞት ፍርድ ያስተላለፈበትን እርምጃ ተከትሎ ነው። ሂዩማን ራይትስ ዎች ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ የተወሰደ እርምጃ ነው ሲልም ተችቶቷል።