May 21, 2024
ዜና

ዘሌንስኪ የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትርን አሰናበቱ

የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሬዝኒኮቭ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሀገሪቱ መሪ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አስታወቁ።

ሚስተር ሬዝኒኮቭ በየካቲት 2022 የሩሲያ አጠቃላይ ወረራ ከመጀመሩ በፊት የመከላከያ ሚኒስቴሩን ሲመሩ ነበር።

ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ በምሽት ንግግራቸው ላይ እንዳሉት ከሆነ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ አዲስ አካሄዶች ያስፈልጋል ጊዜውም አሁን ነው ብለዋል ።

ሚስተር ዘለንስኪ የዩክሬን ግዛት ንብረት ፈንድ የሚመራው ረስተም ኡሜሮቭን የሬዝኒኮቭን ተተኪ አድርገው ሰይመዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት በቴሌግራም የመልእክት መተግበሪያ ላይ በላኩት መልእክት “ሚኒስቴሩ ከወታደራዊ እና በአጠቃላይ ከህብረተሰቡ ጋር አዲስ አቀራረቦችን እና ሌሎች የግንኙነት ቅርፀቶችን እንደሚያስፈልገው አምናለሁ” ብለዋል ።